የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ8ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በየካ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ፣ በጉለሌ ፣ ቂርቆስ እና ልደታ ክ/ከተሞች የሚገኙ እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት ከቴሌ ብር ከአካዉንታችሁ ተቀናሽ በማድረግና ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን በኦን ላይን በ https://landleasedocument.aalb.gov.et/ መግባት መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሰነድ ግዢውን ከታህሳስ 27/2018ዓ.ም እስከ ጥር 12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት መፈፀም ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ ሲፒኦ፣የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበትን ስሊፕ፣መታወቂያ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በአንድ (1) ኤንቨሎፕ በማሸግ ጥር 12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 13/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ታህሳስ 25/2018ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ
በስልክ ቁጥር +251111570595
Website:- https://www.aalb.gov.et/
Portal Link: https://landleasedocument.aalb.gov.et/
አልያም ወደ የቢሮውን የማበራዊ ትስስር ገጿች
https://linktr.ee/addisabababacityland መመልከት ይችላሉ